ለውሃ ዘርፍ አቅም ግንባታ የሚውል የ696 ሚሊየን ብር የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ…!!!

የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከመስኖ ልማት ኮሚሽን ጋር ለ5 ዓመታት (እ.ኤ.አ ከ2021-2025) የሚቆይ በመስኖ ልማት ላይ ያተኮሩ 17 የስልጠና ፕሮግራሞች በመላው ሀገራችን ለሚገኙ ቁጥራቸው 34786 ለሚሆኑ የዘርፉ ባለሙያዎችና አመራሮች ስልጠናዎችን ለመስጠት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱን በኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በኩል የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምሩ ፍቃዱ እንዲሁም በመስኖ ልማት ኮሚሽን በኩል የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር ኢንጂነር ሳሙኤል ሁሴን ተፈራርመዋል፡፡

በመግባቢያ ስምምነቱ ወቅት በኢንስቲትዩቱ እና በኮሚሽኑ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የማኔጅመንት አባላትና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

(EWTI-PRCD-20-5-13 E.C)